ወድ ሰልጣኞቻችን ወደ ማህበራችን የስልጠና ድህረ ገጽ እንኳን በደህና መጣቹ፤ የዚህ ስልጠና አላማ በስራ ቦታ ላይ  የሚደርሰውን ወሲባዊ ትንኮሳና ጥቃት ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት አስተዳዳሪዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ የኮሚቴ አባላት፣ ሰራተኞች እና ግለሰቦች ተግባራዊ ግንዛቤ መፍጠር ነው። ስልጠናው የስርዐተ ጾታ እኩልነትና ፍትሃዊነትን መተግበር፤የሪፖርት አቀራረብ ዘዴዎች የህግ እና ድርጅታዊ ፖሊሲዎች ዕውቀትን በማሻሻል  የመከባበር፤የተጠያቂነትን እና የመቻቻል ባህልን በማጎልበት ደህንነቱ የተጠበቀ  ፍትሃዊ የስራ አካባቢ ለሁሉም እንዲኖር የሚያስችል ነው

ይህ ስልጠና ሶስት ሞጁሎች ሲኖሩት እነዚህም፤

ሞጁል 1፡ መግቢያና የስርዐ-ጾታ እኩልነትና ፍትሃዊነትን መለየትና መተግበር

ሞጁል ፡2 የወሲባዊ ትንኮሳዎች መለየትና መከላከል

ሞጁል፡3 ከወሲባዊ ትንኮሳና ጥቃት ለመጠበቅ ያሉ ህጋዊ ከለላዎች

መልካም የስልጠና ጊዜ፡፡

Course Type: Tutored
Duration: 12 Hours