ይህ ስልጠና ኮምፖስትን ለማዘጋጀት እና ለመጠቀም አስፈላጊ የሆኑ  ሂደቶች፣ መሳሪያዎች እና የመስክ ተግባራትን እውቀት እና ክህሎት ያስጨብጣል። የስልጠናው ዓላማ በተፈጥሮ መንገድ የሚገኙ ተፈጥሯዊ ነገሮችን (Organic Materials) በመጠቀም በምን መልኩ ኮምፖስት ማዘጋጀት እንደሚቻል ማሳወቅ ነው።

ስልጠናው በአጠቃላይ በስድስት ሞጁሎች ተዋቅሯል እነዚህም፦

  • ሞጁል 1 መግቢያ
  • ሞጁል 2 ለኮምፖስት ዝግጅት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
  • ሞጁል 3 ኮምፖስትን ለማዘጋጀት የምንጠቀምባቸው ግብዓቶች
  • ሞጁል 4 የኮምፖስት አዘገጃጀት ዘዴዎች
  • ሞጁል 5 በኮምፖስት ዝግጅት ሂደት የሚደረግ ክትትልa
  • ሞጁል 6 የኮምፖስት አጠቃቀም

መልካም የስልጠና  ግዜ!

Course Type: Tutored
Duration: 8 Hours